የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከአለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ኢንሰቲትዩት እና የሥርዓተ-ምህዳር ፍትሕ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን የCOP-28 ዝግጅት ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
**********
ጥቅምት 7/2/2016 አዲስ አበባ (የፕ.ል.ሚ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከአለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ኢንሰቲትዩት እና የሥርዓተ ምህዳር ፍትሕ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን የCOP-28 ዝግጅት ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
በዱባይ ለሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ COP-28 የመጀመሪያ ምዕራፍ ዝግጅትን የሚጠናቀቅበት እና COP-28 መድረክ ለሚኖረው ድርድር የሚያግዝና የዕውቀት ሽግግር የሚድረግበት የስልጠና መድረክና በተለይም ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት፣ ሲቪል ማህበራት እንዲሁም ከሚዲያዎች ጋር የጋራ ግንዛቤን የሚፈጠርበት ስልጠና ነዉ።
ስልጠናው ሁለት አበይት ዓላማ አለው ያሉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ዋና መሪ እና አስተባባሪ አቶ አባስ መሀመድ ኢትዮጵያን ወክለው በ COP-28 ለሚደራደሩ ተሳታፊዎች ግንዛቤን ለመፍጠር ሲሆን በመድረኩ በሚደረገው ድርድር እንዴት አድርገን ተፅዕኖ መፍጠር እንዳለብን እና የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር የምንሄድባቸው የድርድር ሂደቶች ለማስገንዘብ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መታደጊያ ፋይናንስን በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም የአረንጓዴ የአየር ንብረት ድጋፍ (GCF) የሚመጣውን ፈንድ ለመጠቀም ደግሞ ከሴክተሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመምከር የ(GCF) ድጋፍ ለማግኘት ለሁለተኛ ግዜ እየተዘጋጀ ባለው ሃገራዊ ፕሮግራም ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ያንን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለምትሳተፍበት የ COP-28 መድረክ በሚኖረው ዝግጅት ኢትዮጲያን ወክለው ለሚሳተፊ ባለሞያዎች ስለ ድርድር ምንነት ፣ አካሄድ እንዲሁም ሁሉን የሚያስማማ ሀሳብ በምን መንገድ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚያሳይ ስልጠና ነው የተባለው፡፡ ስልጠናው የዘንድሮም ተሳትፎ ሁለገብና ውጤታማ የምንሆንበት መድረክ እንዲሆን ያስችላል ነው ያሉት አቶ አባስ፡፡
ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆየው ስልጠና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ሲቪል ማህበራት እንዲሁም መንግስታዊ ተቋማት የሚሳተፉበት እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን ከአለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት ኢንሰቲትዩት እና የሥርዓተ ምህዳር ፍትሕ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጄ ነዉ።

© Copyright 2026 Eco-justice Ethiopia | Environmental Justice