ይህ አካል በዋናነት የተቀየሰው የአካባቢ መበከል፣ የደንመጨፍጨፍ፣ የኢንዱስትሪ ብክለት፣ ብክነትና የአየርንብረት ለውጦችን ለመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ የወረዳ ፣ የዞን ፣ የከተማ ፣ የክልል እና የፌዴራል ደረጃዎች ፣ ዳኞች እና ዓቃቤ ሕግ ፣ የመሬት አስተዳደር ሠራተኞች ፣ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ሠራተኞች እና ለሰፊው ሕዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንዲሁም ተጽዕኖ ለመፍጠር ነው ፡፡ ይህ የድርጅት ክፍል በንፁህ አካባቢ የመኖርእና የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም የማግኘት መብታቸው የተጓደለባቸዉ ግለሰቦችን መርዳት ላይ ያተኩራል፡፡ በዚህ አካል ስር ስልጠናዎች ፣ አውደ ጥናቶች ፣ ሴሚናሮች ፣ ምክሮች እና ጥብቅና እንዲሁም የልምድ መጋራት የሚከናወኑ ዋና ተግባራት ናቸው ፡፡
ከዋና ተልዕኮዎቻችን አንዱ ድርጅቱ በራሱ ወይም በሌሎች አጋሮች የተጀመሩ እና የተከናወኑትን የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ በፍርድ ቤት የሚደረጉ ክርክሮችን መደገፍ ነው ፡፡ ከአካባቢ እና ከተፈጥሮ ሀብቶች ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች የእኛ የጥብቅና እና የማስተዋወቂያ ክፍል የሕግ ድጋፍ ፣ የምክር አገልግሎት እና የሕግ ውክልና የማቅረብ ዓላማ አለው ፡፡ ኢኮ-ጀስቲስ ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ህጎችን ወደ ፍርድ ቤቶች ለማምጣት አቅዷል ፡፡ በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ ክፍሎች እስካሁን ድረስ የእነዚህን ሕጎች የፍርድ አተረጓጎም እና ተግባራዊነት ታይትዋል ማለት አይቻልም ፡፡